Search

የኢትዮጵያ ማንሰራራት የ2018 ዓ.ም ግዙፍ ስኬቶች፣ ታሪካዊ ፕሮጀክቶች እና ሁለንተናዊ የከፍታ ማረጋገጫዎች

ረቡዕ ነሐሴ 27, 2018 199

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ይፋ እንዳደረገው ዘንድሮ አምስቱም የጳጉሜ ቀናት "የኢትዮጵያ ማንሰራራት" በሚል ታላቅ መሪ ቃል በድምቀት ይከበራሉ።

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ዴሲሳ በሰጡት መግለጫ እንዳመለከቱት፣ ይህ መሪ ቃል የተመረጠበት ዋና ምክንያት ሀገራችን ኢትዮጵያ በምታደርገው የማንሰራራት ጉዞ ውስጥ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ መሠረት የጣሉ በርካታ የሚጨበጡ ስኬቶች የተመዘገቡበት ዓመት በመሆኑ ነው።

2018 . የኢትዮጵያን ከፍታ የሚያረጋግጡ ግዙፍ ፕሮጀክቶች የተጠናቀቁበት እና አዳዲስ ታላላቅ ሥራዎች የተጀመሩበት ታሪካዊ ዘመን መሆኑን ጠቁመዋል።

ከዚህ በተጨማሪም የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ዙር ምርቃት፣ የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት ግንባታ፣ የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ እንዲሁም የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትና የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታዎች ጅማሮ የዚሁ ታላቅ ዘመን ትሩፋቶች እና የኢትዮጵያ የማንሰራራት ህያው ተምሳሌቶች ናቸው።

በኢኮኖሚው ዘርፍ የተመዘገቡት አስደማሚ ስኬቶችም የሀገራችንን የማስፈጸም አቅም በግልጽ የሚያሳዩ ናቸው። በበጀት ዓመቱ የሀገራችን የገቢ ሰብሳቢነት አቅም በከፍተኛ ደረጃ አድጓል። 

በተመሳሳይ መልኩ በዚሁ የበጀት ዓመት በኢትዮጵያ ታሪክ ከፍተኛው የሆነው የውጭ ገቢ ማግኘት የተቻለ ሲሆን፣ እነዚህ ሁሉ ተስፋ ሰጪ ውጤቶች ኢትዮጵያ ወደ ላቀ የልማትና የከፍታ ላይ መሆኗን በተግባር የሚያረጋግጡ ተጨባጭ አመልካቾች ናቸው።

 

በዓይናለም ሃድራ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: