ለ26ኛ ጊዜ የተዘጋጀው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።
በርካታ የሀገር ውስጥና የውጪ ሀገራት ተሳታፊዎች፣ አምባሳደሮች፣ ተጋባዥ አትሌቶች የሚታደሙበት መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ያዘጋጀው የሩጫ ውድድር ኅዳር 13 ቀን 2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡
ውድድሩ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የገለጸው ፖሊስ፣ ለጋራ ደኅንነት ሲባል ፍተሻ እንደሚኖር የውድድሩ ተሳታፊዎች ተገንዝበው አስፈላጊውን ትብብር ማድረግ እንዳለባቸው አስገንዝቧል።
የወድድሩ ተሳታፊዎች በሚያልፉት አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች እንደ ከዚህ ቀደሙ ከፀጥታ ኃይሉ ጎን በመቆም ትብብራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉም ፖሊስ ጥሪውን አስተላልፏል።
ውድድሩ የከተማችንን ዋና ዋና መንገዶች የሚያካልል በመሆኑ ሩጫው ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ ያስታወቀው ፖሊስ፣ ውድድሩ በሠላም እንዲጠናቀቅ የፀጥታ አካላት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቅቀው ወደ ሥራ መግባታቸውን አመላክቷል።
ውድድሩ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅም የሚዘጉ መንገዶች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡-
👉 ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ (ኦሎምፒያ አደባባይ)
👉 ከጥላሁን አደባባይ ወደ ሳንጆሴፍ መብራት (ጥላሁን አደባባይ) ለከባድ ተሽከርካሪ አጎና ሲኒማ
👉 ከአፍሪካ ህብረት መብራት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ጥይት ቤት መስቀለኛ)
👉ከፓርላማ መብራት ወደ ኮንሰን መታጠፊያ (ፓርላማ መብራት)
👉 ከኮንሰን መታጠፊያ ወደ ቅዱስ ገብርኤል (ኮንሰን መታጠፊያ)
👉 ከጥይት ቤት ወደ ቅዱስ ገብርኤል በጀርባው (ጥይት ቤት መታጠፊያ)
👉 ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስና ካዛንቺስ ቶታል (ሴቶች አደባባይ)
👉 ከ22 አደባባይ ወይም ዘሪሁን ህንፃ ወደ ቅዱስ ዑራኤል አደባባይ (ዘሪሁን ህንፃ መስቀለኛ)
👉 ከፒኮክ አዲሱ መንገድ ወደ ዑራኤል አደባባይ (ፒኮክ መብራት)
👉 ከጋዜቦ አደባባይ ወደ ደንበል (ጋዜቦ አደባባይ)
👉 ከቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን መስቀለኛ ወደ ለገሃር መብራት (ቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክርሰቲያን)
👉 ከላንድ ማርክ ሆስፒታል መታጠፊያ ገነት ሆቴል ወይም ወደ ገነት መብራት (ላንድ ማርክ ሆስፒታል መስቀለኛ)
👉 ከጠማማ ፎቅ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ጠማማ ፎቅ መስቀለኛ)
👉 ከአፍሪካ ህብረት መብራት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ሜክሲኮ ጥይት ፋብሪካ መስቀለኛ )
👉 ከፈረሰኛ መብራት ወደ ጨፌ ሜዳ (ፈረሰኛ መብራት)
👉 ከሞላ ማሩ መስቀለኛ ወደ ጌጃ ሰፈር (ጌጃ ሰፈር መስቀለኛ)
👉 ከከፍተኛ ፍ/ቤት አደባባይ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ከፍተኛ ፍ/ቤት አደባባይ)
👉 ከሠንጋ ተራ 40/60 ወደ ሠንጋ ተራ መብራት (ሠንጋ ተራ 40/60 መታጠፊያ)
👉 ከጎማ ቁጠባ መብራት ወደ ብ/ቲያትር (ጎማ ቁጠባ መብራት)
👉ከሜትሮሎጂ መታጠፊያ ወደ ፖስታ ቤት መብራት (ሜትሮዎሎጂ መታጠፊያ)
👉 ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ኢምግሬሽን (ጥቁር አንበሳ ሼል)
👉ከጎላ ቅዱስ ሚካኤል መስቀለኛ ወደ ኢምግሬሽን (ጎላ ቅዱስ ሚካኤል መስቀለኛ)
👉 ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ አገር አስተዳደር መብራት (ቴዎድሮስ አደባባይ)
ከንጋቱ 11:30 - ሰዓት ጀምሮ ውድድሩ እስከሚጠናቀቅ የተጠቀሱት መንገዶች የሚዘጉ ሲሆን፣ በተጨማሪም በተገለጹት መስመሮች ላይ ዛሬ ቅዳሜ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ ለአጭርም ይሁን ለረጅም ጊዜ ተሽከርካሪ ማቆም የተከለከለ መሆኑ ተገልጿል።
የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘት 011 1110111 ወይም ነጻ የስልክ መስመር 990 መጠቀም እንደሚቻልም አስታውቋል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: