የኢትዮጵያ ሠራዊት ተቋማት ኮንፌዴሬሽን "በኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም አንደራደርም" በሚል መሪ ቃል የፓናል ውይይት አካሄደ።
የኢትዮጵያ ሠራዊት ተቋማት ኮንፌዴሬሽን በኢትዮጵያ የቀይ ባህር በመመለስ ሂደት ዙሪያ "በኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም አንደራደርም" በሚል መሪ ቃል የፓናል ውይይት አካሄዷል።
በመድረኩ ላይ የሀገር መከላከያ ሠራዊት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮሎኔል ቢረሳው ሽፈራው እና አምባሳደር ዲና ሙፍቲን ጨምሮ የቀድሞ ሠራዊት አባላትና የክብር አባላት ተገኝተዋል።
በፓናል ውይይቱ ላይ የተሳተፉት የቀድሞ የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎችና የፖሊስ ሠራዊት አባላት በብሔራዊ ጥቅም ላይ እንደማይደራደሩ ገልጸው፤ ኢትዮጵያ የጀመረችውን የልማትና የብልጽግና ጉዞ ለማደናቀፍ የሚጥሩ ኃይሎችን ለማምከን ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጎን በጋራ እንደሚቆሙ አረጋግጠዋል።
ከውይይቱ በተጨማሪም "የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ትናንት፣ ዛሬና ነገ"በሚል ርዕስ በ ታደሰ ብሩ (ዶ/ር) ጥናታዊ ጽሑፍ ቀርቦ ኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባሕር በመመለስ ሂደት ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።
በኤዶሚያስ ንጉሴ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: