Search

"ዛሬ የተፈረመው የቤት መግዣ ብድር ፋይናንስ ስምምነት የኢትዮጵያን የቤት አቅርቦት ታሪክ የሚቀይር ግዙፍ ዜና ነው” - አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ

ሓሙስ ነሐሴ 28, 2018 122

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) መካከል በዛሬው ዕለት የተደረገው የቤት መግዣ ብድር (ሞርጌጅ) ፋይናንስ ስምምነት የኢትዮጵያን የቤት አቅርቦት ታሪክ የሚቀይር ግዙፍ ዜና መሆኑን የምጣኔ ሀብት ባለሙያው አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ ገለጹ።

ባለሙያው በኤክስ ገጽ ባጋሩት መልዕክት፣ የሞርጌጅ ፋይናንስ ጉዳይ ለበርካታ ዓመታት ክርክር ሲደረግበት የቆየና እምብዛም ለውጥ ያልታየበት እንደነበር አስታውሰዋል። የዛሬው ስምምነት ግን ይህን ታሪክ የሚቀይር መሆኑን በመጥቀስ፣ ይህንን ታሪካዊ እርምጃ ዕውን ላደረጉት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) የእንኳን ደስ አለዎ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ይህ የብሔራዊ ባንክ እና የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን አጋርነት፣ የዜጎችን የተመጣጣኝ ዋጋ የቤት ፍላጎት ለማሟላት የተወሰደ ትልቅ እርምጃ መሆኑን አብራርተዋል።

በተለይም መንግሥት በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ውስጥ ለኢትዮጵያውያን ለማቅረብ ላቀደው 1.5 ሚሊዮን ተመጣጣኝ ቤቶች ግንባታ ስኬት ስምምነቱ እጅግ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት አጽንኦት ሰጥተዋል።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: