"ለስኬታማ ሀገራዊ ምክክር የምሁራን ሚና"በሚል መሪ ሀሳብ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ያዘጋጀው የምክክር መድረክ በባህርዳር ተካሂዷል።
በመድረኩ በአማራ ክልል የሚገኙ አስሩ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ምሁራን ታድመዋል።
በወቅት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ (ዶ/ር)፤ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራን ሀገራዊ ችግሮችን በዘላቂነት በመግባባት ለመፍታት የላቀ ሚና እንዳላቸው አንስትዋል።
ምክክር የፖለቲካ ልዩነቶችን ለመፍታት፣ በመንግሥት እና በሕዝብ መካከል መተማመን ለማስፈን፣ የዴምክራሲ ስርአትን ለማጠናከር እንዲሁም ግጭቶችን ለማስወገድ ጉልህ ሚና ያለው ስለመሆኑ አንስገንዝበዋል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽንም ምክክር የኢትዮጵያ ፖለቲካ ባህል እንዲሆን እየሠራ ነው ብለዋል።
ለሀገራዊ ምክክሩ ስኬታማነት የምሁራን ሚና የላቀ በመሆኑ መድረኩ ማስፈለጉን ጠቁመው፤ በቀጣይ ምሁራን በምክክር ሒደቱ ሰፊ ተሳትፎ ሊያደርጉ እንደሚገባ አመላክተዋል።
በራሔል ፍሬው