Search

አፍሪካውያን የባለብዙ ወገን የትብብር መድረክን ማጠናከር ይገባቸዋል

እሑድ ጥቅምት 16, 2018 48

አፍሪካውያን በባለብዙ ወገን የትብብር መድረክ ላይ አቅማቸውን ማጠናከር እንደሚገባቸው ተገለጸ።

“አፍሪካ በተለዋዋጩ የዓለም ሥርዓት” በሚል መሪ ሀሳብ በተካሄደው 11ኛው የጣና ፎረም ላይ በባለብዙ ወገን ትብብር ዙሪያ የፓናል ውይይት ተካሄዷል።

አፍሪካ በሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ላይ የባለብዙ ወገን የትብብር መድረክን ማጠናከር አለባት ተብሏል።

በተለይም አህጉራዊ ተቋማትን ማጠናከር እንደሚገባ ነው በውይይቱ ላይ የተነሳው።

በአፍሪካ የሚታዩ ግጭቶችንም አካታች በሆነ መልኩ መፍታት እንሚገባ ተጠቁሟል።

ለ3 ቀናት በባሕር ዳር እና በአዲስ አበባ የተካሄደው በአፍሪካ የሰላምና ደህንነት ላይ የሚመክረው የጣና ፎረም በዛሬው ዕለት ተጠናቅቋል።

በሙሉ ግርማይ

#ebcdotstream #ethiopia #addisababa #tanaforum #multilateralcooperation