ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የተነሱ ዋና ዋና ጥያቄዎች መካከል፦ ማክሰኞ ጥቅምት 18, 2018 749 ኢትዮጵያን ለማዳከም ከታሪካዊ ጠላቶች ጭምር ተልዕኮ በመቀበል የባንዳነት ተግባር ላይ የተሰማሩ ፀረ ሰላም ኃይሎች ላይ ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ ምን እየተሰራ ነው? ከሕዝቡስ ምን ይጠበቃል? የፕሪቶሪያውን ስምምነት ወደ ጎን በመተው የትግራይን ሕዝብ ወደ ጦርነት እና ስቃይ ለማስገባት የሚሞክረው የሕወሓት ቡድን አሁን ደግሞ ከሻዕቢያ ኃይሎች ጋር ጭምር የሀገሪቱን ሰላም ለማወክ እየሰራ በመሆኑ መንግሥት ክልሉን ሰላማዊ ለማድረግ ምን እየሰራ ነው? የክልሉ አሁናዊ የፖለቲካ፣ የሰላም እና ፀጥታ ሁኔታስ ምን ይመስላል? የሀገራዊ ምክክር ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሷል፤ ይህ ዕድል ውጤታማ እንዲሆን ከማን ምን ይጠበቃል አንሳተፍም ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በተመለከተ የመንግሥት አቋም ምንድን ነው? መልካም አስተዳደር ከማስፈን እና ብልሹ አሰራሮችን ከማረም አኳያ ከመንግሥት በኩል በቀጣይ ምን ሥራዎች ይከናወናሉ? 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በተለመደው የምርጫ ሂደት ይከናወናል ወይስ በአዲስ መልክ ከሀገራዊ ምክክሩ መጠናቀቅን ተከትሎ በሚወሰዱ ምክረ ሀሳቦች በአዲስ መልክ ነው የሚካሄደው? ቀጣዩ ምርጫ ሰላማዊ እና ተዓማኒ በሆነ መልኩ እንዲደረግ ምን እየተሰራ ነው? ከሕዝቡስ ምን ይጠበቃል? የባህር በር ፍላጎታችን ከጎረቤታችን ኤርትራ ጋር ባለው ግንኙነት አውድ ውስጥ እንዴት ይታያል? በመንግሥት በኩል ለወንድም የአፍሪካ ሀገራት የማብራራት ሂደቱ ምን ይመስላል የሚለው ቢብራራ? የትምህርት ጥራት ችግርን ለመፍታት እና የተማሪዎችን የማለፍ ምጣኔ ለመጨመር ምን እየተሰራ ነው? የማዕድን ዘርፍ ፕሮጀክቶችን በመገንባት የተጀመሩ ሥራዎችን ማስፋፋት ላይ ምን ተግባራት እየተከናወኑ ነው? አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: Send ተያያዥ ዜናዎች: ምርጫውን ለመታዘብ 55 ድርጅቶች ተመዝግበዋል - ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሓሙስ ሚያዝያ 15, 2018 ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ከ50 ሚሊዮን በላይ መራጮች ተመዝግበዋል - ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሓሙስ ሚያዝያ 15, 2018 "የትግራይ ወጣት የፖለቲካ ሴራዎችን ተረድቷል፤ ከአሁን በኋላ የጦርነት መሣሪያ አይሆንም"፦ የቀድሞዋ አፈ-ጉባኤ ኬሪያ ኢብራሂም እሑድ ሚያዝያ 11, 2018 የአፋብን ወታደራዊ አዛዥ ኮማንዶ ፍቅሩ ሙሉዬ የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀበለ ሰኞ መጋቢት 21, 2018
5 "ከመስከረም 2018 ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መንግሥት ወስኗል"፦ የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሰኞ ነሐሴ 12, 2017 28038