አዲስ አበባ ሰፊ አቅም የሚጠይቁ እን ያሉ ግዙፍ ካፒታል ያላቸውን የፕሮጀክት ሥራዎች በብቃት በማከናወን ምሳሌ መሆን ችላለች ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይ ተናገሩ።
በጥራት ተገንብተው የተጠናቀቁት የኮሪደል ልማቶች፣ ሆስፒታሎች እና የትምህርት ተቋማት፣ የከተማ ግብርና እንዲሁም የቦሌ አራብሳ ፍሳሽ ማጣሪያ ግዙፍ ፕሮጀክቶች በአጭር ጊዜ ተጠናቅቀው ለአገልግሎት መዋላቸውን አስታውሰዋል።
አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬሽን ሴንተር፣ መዝናኛ ስፍራዎችን፣ የዐድዋ መታሰቢያ ፣ አብርሆት ቤተ-መፅሐፍት ፣ ግዙፍ መንገዶች ፣ፓርኮች እና ድልድዮችን ጨምሮ የተለያዩ ግዙፍ ፕሮጀክቶች በፍጥነት ጀምሮ የመጨረስ አቅምን ማሳያዎች ናቸው ብለዋል።
ፕሮጀክቶቹ በኢኮኖሚ እና ማኀበራዊ ልማት ላይ ጉልህ ሚና ያላቸው ሲሆኑ፤ ለዜጎች ከፍተኛ የሥራ ዕድልን የፈጠሩ መሆናቸውን አንስተዋል
አዲስ አበባን መልሶ የማልማት አላማ የሆኑት ፕሮጀክቶች በአጭር ጊዜ እውን እንዲሆኑ የከተማ አስዳደሩ ጥብቅ ክትትል እና ጠንካራ የሥራ አመራር ስርዓቱ ወሳኝ ሚና ነበረው ሲሉም አስረድተዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ የተሰሩ የሜጋ ፕሮጀክቶች በኢትዮጵያውያን አማካሪዎች እና ተቋራጮች እንዲሁም በሀገር ውስጥ የዲዛይን ባለሙያዎች የተሰሩ መሆናቸው ለሌሎች ሥራዎችም አቅም እንዳለን ማሳያ ነው ብለዋል።
በሄለን ተስፋዬ