የጉምሩክ ኮሚሽን እና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (EBC) ስትራቴጅካዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት በዛሬው ዕለት ተፈራርመዋል ።
ስምምነቱን የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ (ዶ/ር) እና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ቢንያም ኤሮ ፈርመውታል።
የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ፤የጉምሩክ ኮሚሽን የገቢና የወጪ ንግድ በማሳለጥ እንዲሁም ገቢን በመሰብሰብ የኢትዮጵያን ኹለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ እየተጋ መሆኑን ገልጸዋል።
የህግ ተገዥነትን ለማረጋገጥ እና የአገልግሎት አሰጣጡን ተደራሽ ለማድረግ የግንዛቤ ፈጠራ ሥራዎች ወሳኝ መሆናቸውን ኮሚሽነሩ ገልጸው ይህንን ዕውን ለማድረግ የሚዲያ ሚና አይተኬ ነውም ብለዋል።
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ቢንያም ኤሮ በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ህብረ ብሔራዊ አንድነትን ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችሉ ሥራዎችን እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል።
የታክስ እና የጉምሩክ ህግ ተገዥነቱ ያደገ ማህበረሰብን ለመፍጠር የሚያስችሉ ሥራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል ስምምነቱ ወሳኝ መሆኑንም ዋና ሥራ አስፈጻሚው አብራርተዋል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: