Search

የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት

ረቡዕ ጳጉሜን 04, 2018 75

ዛሬ በኅብር ቀን አሮጌውን ዓመት አልፈን ወደ አዲስ ዓመት መሸጋገርን ከሚያበስሩ ውብ እና ህብራዊ ባህሎቻችን መካከል የሆኑትን የአበባአየሽ ወይ፣ የአሸንዳ፣ ጎቤ፣ ሽኖዬ፣ ሻደይ ጭፈራዎች በከተማችን በታሪካዊው የአድዋ ድል መታሰቢያ በድምቀት ተከብረዋል።

ኢትዮጵያ የበለፀገ የህብረተሰብ ሀብት ክምችት ያላት ሀገር ናት። የመደመር መንግሥትም እነዚህን ሀብቶች በመጠበቅ፣ በመንከባከብና በማልማት ለሀገር እድገትና ለህብረተሰብ ልማት ማዋል ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው።

ህብረብሔራዊት በሆነችው ከተማችንም ውብ ኢትዮጵያዊ ባህሎቻችን ጎልተው እንዲወጡ፣ ከባህሉና እሴቱ ማግኘት የሚገባንን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጥቅም እንዲያስገኙ እና የቱሪዝም መስህብ እንዲሆኑ እየሰራን እንገኛለን።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: