Search

ከብድር ተቀባይነት ወደ ዓለም አቀፍ ኢንቨስተርነት

ረቡዕ ጳጉሜን 04, 2018 18

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚና በውስጥ ገበያ ብቻ የተወሰነ ነው የሚለው የተለመደ እሳቤ አሁን ላይ ታሪክ እየሆነ መጥቷል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተቋማቱን አቅም በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ፣ ከዕለት ተዕለት የአስተዳደር ተግባር አልፎ ድንበር ተሻጋሪ የኢንቨስትመንት ኃይል በመሆን አዲስ የኢኮኖሚ ምዕራፍ ከፍቷል።

ይህ ስትራቴጂየያዊ እርምጃ ብሔራዊ ተቋማቱ በአፍሪካ ገበያ ጭምር ጠንካራ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ሰፊ ዕድል የፈጠረ እና ዓለም አቀፍ ተጽዕኖ አድራጊነታቸውን ያረጋገጠ ነው።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋነኛ ራዕይ የተቋማቱን አቅም ማጎልበት ብቻ ሳይሆን፣ '3 ስትራቴጂ' በመመራት በአፍሪካ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ፣ አትራፊ እንዲሁም ዘላቂ እሴት ፈጣሪ ማድረግ ነው።

በርካታ ግዙፍ የመንግሥት ልማት ድርጅቶችን በሥሩ የሚያስተዳድረው ይህ የሉዓላዊ ሀብት ፈንድ፣ ይህንን ስትራቴጂያዊ አቅጣጫ በመከተል ተቋማቱን ከውስጥ አቅም ግንባታ ባሻገር በዓለም አቀፍ መድረክ የካፒታል እና የቴክኖሎጂ አጋርነትን እንዲፈጥሩ እያደረጋቸው ይገኛል።

ይህ ትልቅ ተቋማዊ ራዕይ በወረቀት ላይ ብቻ የተወሰነ ሳይሆን፣ በተግባርም ተጨባጭ ውጤት እያመጣ ነው።

ለዚህም ዋነኛ ማሳያው የመንግሥት ልማት ድርጅቶች በተለይም በአቪዬሽን፣ በቴሌኮም እና በሎጂስቲክስ ዘርፎች በታንዛኒያ እና በናይጄሪያ ገበያዎች ገብተው ገቢ ማመንጨት መጀመራቸው ነው።

ከዚህም ባሻገር፣ ከሰባት አስርት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም አቀፍ የአክሲዮን ገበያ ላይ የባለቤትነት ድርሻን ማረጋገጥ መቻሉ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ስትራቴጂ ትልቁ የስኬት ማሳያ ሆኖ ተመዝግቧል።

ይህ ዓይነቱ ድንበር ተሻጋሪ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ኢትዮጵያን ከብድር ተቀባይነት ወደ ዓለም አቀፍ የካፒታል ባለቤትነት እና ኢንቨስተርነት እያሸጋገራት ይገኛል።

አህጉራዊ ተወዳዳሪነትን በተግባር በማረጋገጥ፣ ጠንካራ የውጭ ምንዛሪ ማስገኛ መንገዶችን በማስፋት እና ብሔራዊ ሀብት በማፍራት ረገድ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው።

የዛሬ ተቋማትን አሠራር በማዘመን የነገ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪዎችን በተጨባጭ መፍጠር ተችሏል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የሕዝብ ንብረት የሆኑ ተቋማትን በዘመናዊ የኮርፖሬት አመራር በአግባቡ በመምራት የዛሬን ውጤት አጉልቶ፣ የነገን ብሔራዊ ሀብት እያረጋገጠ ይገኛል።

መልካም አዲስ ዓመት!

በለሚ ታደሰ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: