ይቅርታ የተደረገላቸው ታራሚዎች በማረሚያ ቤት ቆይታቸው መልካም ስነምግባር ያላቸውና ፀባያቸው የታነፀ መሆኑን በማረሚያ ቤት መረጋገጡን የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ቢሮ ኃላፊ አቶ ጉዮ ዋሪዮ ተናግረዋል።
ይቅርታ የተደረገላቸው ታራሚዎች 2ሺ 518 ወንዶች እና 217 ሴቶች ናቸው። ሕጋዊ አሠራርን መሰረት በማድረግ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ለታራሚዎች ይቅርታ ማደረጉንም የቢሮው ኃላፊ ገልፀዋል።
ይህም የማህበረሰቡን ሰላምና ፀጥታ ለማፅናት እንደሚያስችልም ነው ያረጋገጡት።
ከእድሜ ልክ እስከ 12 አመት እና ከዚያ በላይ ፍርደኞች በዚህ ይቅርታ ተጠቃሚ መሆናቸውን ኃላፊው ተናግረዋል።
የሞት ፍርድ የተወሰነባቸው እና ከተፈቱ በኋላ ድጋሚ ወንጀል የፈፀሙ በዚህ ይቅርታ ተጠቃሚ እንደማይሆኑ ኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ቢሮ ኃላፊ አቶ ጉዮ ዋሪዮ በመግለጫቸው አስረድተዋል።
በጌታቸው ባልቻ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: