Search

ኡጋንዳ በዓመት 1.2 ሜትሪክ ቶን ወርቅ የሚያመርት ማቀነባበሪያ ከፈተች

ረቡዕ ነሐሴ 14, 2017 1855

ኡጋንዳ በምስራቃዊ የሀገሪቱ ክፍል 250 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተገነባውን ግዙፍ ወርቅ የሚያመርት የማዕድን ማውጫ ከፍታለች።

አዲሱ የወርቅ ማቀነባበሪያ ወደ ሥራ የገባ ሲሆን፣ በእየለቱ 5 ሺህ ቶን ወርቅ አዘል ግብዓትን የማጣራት እንዲሁም በዓመት 1.2 ሜትሪክ ቶን የጠራ ወርቅ የማምረት አቅመ እንዳለው ተገልጿል።

የማዕድን ማምረቻው ዩጋንዳ ከቻይና ጋር በባለቤትነት የያዘችው ሲሆን፤ የአፍሪካዊቷን ሀገር የወርቅ ወጪ ንግድ በእጅጉ እንደሚያሳድገው አፍሪካን ቢዝነስ ኢንሳይደር ዘግቧል።

ወርቅ የኡጋንዳ ትልቁ የውጭ ምንዛሪ አስገኚ ምርት ሲሆን ... 2024 ሀገሪቷ ከወርቅ 3.4 ቢሊዮን ዶላር የወጪ ንግድ ገቢ አግኝታለች።

ይህም ከሀገሪቱ አጠቃላይ የወጪ ንግድ 37 በመቶ ያህሉን የሚሸፍን መሆኑ ታውቋል።

የኡጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ "በማዕድን ዘርፉ ለመንሰራራት እንደ ወርቅ፣ ሊቲየም ሌሎች ማዕድናትን ሙሉ ሙሉ እሴት በመጨመር ለገበያ ማቅረብ አለብን" ብለዋል።

በጌትነት ታደሰ

#EBC #ebcdotstream #Gold #mining