Search

የሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክቶችን ከአጣብቂኝ ውስጥ በማውጣት ለፍጻሜ የማድረስ ብቃት የተረጋገጠበት ነው

ረቡዕ ነሐሴ 14, 2017 132

እንደ ሀገር ከተገነቡ ሜጋ ፕሮጀክቶች መካከል ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ከነበረበት አጣብቂኝ በማውጣት ለፍፃሜ የማድረስ ብቃት የተረጋገጠበት መሆኑን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ የትምጌታ አስራት ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያ በተለያዩ ከህንፃ፣ ከመሰረተ ልማት እንዲሁም ከቱሪዝም መዳረሻ ፕሮጀክቶች ባሻገር፣ በመንግስት እና በግሉ ዘርፍ በአጋርነት የሚሰሩ ፕሮጀክቶችን ጭምር በፍጥነት እና በጥራት፤ ዘመን ተሻጋሪ በሆነ መልኩ በማጠናቀቅ ላይ እንደምትገኝ ተናግረዋል፡፡

በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች በመገንባት ላይ የሚገኙት የቱሪዝም መዳረሻዎች የነገንም ትውልድ ተሳቢ አድርገው የተገነቡ መሆናቸውን ነው ሚኒስትር ዴኤታው የገለጹት፡፡

በሀገሪቱ ትኩረት ተሰጥቶ እየተከናወኑ ካሉ ፕሮጀክቶች መካከል የፍጥነት መንገድ አንደኛው መሆኑን ጠቅሰው፤ በሞጆ ሀዋሳ የፍጥነት መንገድ ግንባታ ከባቱ እስከ አርሲ ነጌሌ ያለው ክፍል በቅርቡ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን ጠቁመዋል፡፡

ሜጋ ፕሮጀክቶችን ሰርቶ ከማጠናቀቅ ባለፈ ለሌላ ፕሮጀክቶች ሀገራዊ አቅም የሚገነባባቸው መሆናቸውንም ነው ያነሱት፡፡

ከዚህ ባለፈም ሜጋ ፕሮጀክቶች የአሰሪዎችን እና የሰራተኞችን የሥራ ባሕል እየቀየሩ መምጣታቸውን ገልጸው፤ ለዚህም ማሳያ የተያዙ ፕሮጀክቶች በፍጥነት መጠናቀቃቸው ነው ብለዋል፡፡

በንፍታሌም እንግዳወርቅ

#EBC #ebcdotstream #Ethiopia #megaprojects