Search

ኢራን በኒዉክለር መርኃ ግብሯ ዙሪያ የተቋረጠዉን ድርድር መቀጠል እንደምትፈልግ ገለፀች

ረቡዕ ነሐሴ 14, 2017 146

ኢራን ከምዕራባዉያን በተለይም ከእስራኤል ጋር በሚያወዛግባት እና ግጭት ዉስጥ በከተታት የኒዉክለር መርኃ ግብሯ ዙሪያ የተቋረጠዉን ድርድር መቀጠል እንደምትፈልግ አስታወቀች፡፡

የሀገሪቱ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እስማኤል ባጊ፤ ኢራን የኒዉክለር መርኃ ግብሯን ፈጽሞ አታቆምም ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ሆኖም ግን በምዕራባዉያን የተጣሉባት ማዕቀቦች የሚነሱ ከሆነ ድርድሩን በመተማመን ላይ በተመሰረተ መልኩ ለመቀጠል ዝግጁ ናት ብለዋል፡፡

በኒዉክለር መርኃ ግብሩ ዙሪያ ከአለማቀፉ የአቶሚክ ኃይል ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆኗንም ቃል አቀባዩ አረጋግጠዋል፡፡

በቀጣዩ ሳምንትም በኢራን እና በኤጀንሲዉ መካከል የተቋረጠዉ ድርድር እንደገና ሊጀመር ይችላል ነው ያሉት፡፡

ከምእራባዉያን በተለይም ከእስራኤል ጋር ከእስርት ዓመታት በላይ የዘለቀዉ የኢራን የኒዉክለር መርሀ ግብር ዉዝግብ ተባብሶ፤ ባለፈዉ ሰኔ ወር ወደ ሀይል እርምጃ መሸጋገሩን አፍካ ኒውስ በዘገባው አስታውሷል፡፡ 

#ebc #ebcdotstream #Iran #Nuclear