Search

ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል ሀገራትን የጋራ ራዕይ ለማሳካት ቁርጠኛ ናት - ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)

ዓርብ መስከረም 01, 2019 123

ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል ሀገራትን የጋራ ራዕይ እውን ለማድረግ ከፍተኛ ቁርጠኝነት እንዳላት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (/) አስታወቁ።

በብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (/) የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ፣ በሕንድ ሙምባይ ከተማ እየተካሄደ ባለው 2ኛው የብሪክስ የገንዘብ ሚኒስትሮች እና የማዕከላዊ ባንክ ገዥዎች ስብሰባ ላይ ተሳፏል።

"ለጽናት፣ ለፈጠራ፣ ለትብብር እና ለዘላቂነት መገንባት" በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ጉባኤ፣ በብሪክስ አባል ሀገራት ኢኮኖሚ ላይ የሚስተዋሉ ቁልፍ ተግዳሮቶች እና ዕድሎች በስፋት ተዳስሰዋል።

/ ኢዮብ በዚሁ ወቅት ኢትዮጵያ እየተገበረችው ያለው የፊስካል እና የገንዘብ ፖሊሲ እንዲሁም የምንዛሬ ተመን ለውጡን ጨምሮ በዘርፉ የወሰደችው ስር ነቀል የማሻሻያ እርምጃ ኢኮኖሚው የተለያዩ ተግዳሮቶችን እንዲቋቋም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ገልጸዋል።

የብሪክስ አባል ሀገራትን የፋይናንስ ደህንነት ለመጠበቅ ባለመው የመጠባበቂያ ክምችት ስምምነት ላይ የተደረገውን ማስተካከያ አድንቀው፣ ይህ አካሄድ ጠንካራ የጋራ ፋይናንስ ምንጭ እንደሚፈጥር ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

በሌላ በኩል፣ አዳዲስ አባላት ወደ ቡድኑ የሚቀላቀሉበት ሂደት የእያንዳንዱን ሀገር የዕድገት ደረጃ፣ የፋይናንስ ፍላጎት እና የመሸከም አቅም ግምት ውስጥ ማስገባት እንዳለበት አሳስበዋል።

ኢትዮጵያ ለብሪክስ የጋራ ራዕይ ስኬት ያላትን ቁርጠኝነት የገለጹት ብሔራዊ ባንክ ገዥው፣ ኢትዮጵያ ስትራቴጂያዊ ግቦቿን ለማሳካት ከቡድኑ ጋር በቅንጅት ለመሥራት ያላትን ዝግጁነት ዳግም አረጋግጠዋል።

በላሉ ኢታላ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: