Search

የመደመር ጽንሰ ሀሳብ ለውጡን ለመድፈቅ የተደረጉ ሙከራዎችን ለማክሸፍ ትልቅ አበርክቶ ነበረው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ረቡዕ ነሐሴ 14, 2017 128

የመደመር ጽንሰ ሃሳብ ሀገራዊ ለውጡን ለመድፈቅ የተደረጉ ሙከራዎችን ለማክሸፍ ትልቅ አበርክቶ ነበረው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ "የመደመር መንግሥት" የተሰኘውን አዲስ መጽሐፍ በተመለከተ ባደረጉት ቃለ መጠይቅ፤ መደመር ንድፈ ሐሳብ ብቻ ሳይሆን በሂደት እየዳበረ እና እየጎለበተ የመጣ በድካም የተገኘ ፅንሰ ሐሳብ ነው ብለዋል።

ሀገራዊ ለውጡን ለመድፈቅ የተደረጉ ሙከራዎችን ለማክሸፍ ጽንሰ ሃሳቡ ትልቅ አበርክቶ እንደነበረውም ተናግረዋል፡፡

ዋጋ የተከፈለበት ለውጥ ሀቀኛ ለውጥ ሆኖ የሚጠበቅበትን ውጤት እንዲያመጣ አቅጣጫ የተቀመጠው በዚሁ ጽንሰ ሃሳብ ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

በለውጡ መንገድ ለውጡን ሊቀለብሱ፣ ሊጠልፉና ተሃድሷዊ በሆነ መንገድ ሊያስኬዱ የሚፈልጉ ኃይሎች እንዳሉ ተረድተን ሊደርሱብን በማይችሉት ፍጥነት ብንጓዝ አቅም እያነሳቸው እየተንጠባጠቡ ይቀራሉ በሚል በጋራ የወሰንበት ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

የመደመር መንግሥት ከብዙ ድካም በኋላ የተገኘ መሆኑን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ምናልባትም በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ ታሪክ መንግሥታት የሚመሩበት ንድፍ እና ሰነድ በግልጽ በዚህ መልክ ተሰንዶ ለሕዝባቸው ያቀረቡበት እንዳልተገኘ አብራርተዋል።

#EBC #ebcdotstream #PMAbiy #PMOEthiopia #Medemer #Yemedemermengist