Search

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ 70ኛ አጠቃላይ ጉባኤ ላይ እየተሳተፈች ነው

ረቡዕ መስከረም 06, 2019 125

ኢትዮጵያን ጨምሮ 181 አባል ሀገራት የተሳተፉበት የዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ (IAEA) 70 አጠቃላይ ጉባኤ በኦስትሪያ ቪየና በይፋ መካሄድ ጀምሯል።

በጉባኤው መክፈቻ ላይ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ሚስተር ራፋኤል ግሮሲ ባለፈው ዓመት የተከናወኑ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ሥራዎችን እንዲሁም ያመጧቸውን በጎ ተጽዕኖዎች አብራርተዋል።

በጉባኤው ላይ የየሀገራቱ ተወካዮች ከኒውክሊየር ደህንነት፣ ጥበቃ እና ቴክኖሎጂ ትግበራ ጋር የተያያዙ እንቅስቃሴዎችን ለማጠናከር በጥልቀት እንደሚመክሩ ተነግሯል።

በተጨማሪም ኤጀንሲው 2025 ዓመታዊ ሪፖርቱን፣ 2027 የበጀት ማሻሻያን እና የፋይናንስ ሪፖርቶችን ገምግሞ የአስተዳደር ቦርድ አባላትን እንደሚመርጥ ተገልጿል።

 

በዚህ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ በጄኔቫ የኢትዮጵያ ቋሚ መልክተኛ ጽሕፈት ቤት ምክትል ሚሲዮን መሪ አምባሳደር ኃይለሥላሴ ሱባ እንዲሁም ሁለተኛ ጸሐፊ / ቤተልሔም መኮንን የኢትዮጵያን ልዑክ በመምራት ተሳትፎ እያደረጉ እንደሚገኙ የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን መረጃ አመልክቷል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: