Search

የትምህርት ሚኒስቴር የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የዩኒቨርሲቲ ምደባን ይፋ አደረገ

ረቡዕ መስከረም 06, 2019 221
የትምህርት ሚኒስቴር የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ወደ ዩኒቨርሲቲዎች የመመደብ ሂደቱን ፍትሐዊነት፣ ግልጽነትና እኩል ዕድልን ባረጋገጠ መልኩ ማጠናቀቁን ይፋ አድርጓል።
ምደባው የተማሪዎችን ውጤት፣ ምርጫ፣ የዩኒቨርሲቲዎች ቅበላ አቅም፣ የፆታ ሚዛን እንዲሁም የህብረ ብሔራዊነት ስርጭትን ታሳቢ ያደረገ ነው ተብሏል።
በዚህም 500 እና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎች በመጀመሪያ ምርጫቸው የተመደቡ ሲሆን፣ ማየትና መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች ደግሞ አስፈላጊው ድጋፍ በሚደረግላቸው ዩኒቨርሲቲዎች መመደባቸው ተገልጿል።
ተማሪዎችም የተመደቡበትን ዩኒቨርስቲ ለመመልከት በዚህ ሊንክ https://student.ethernet.edu.et/view-placement መመልከት እንደሚችሉ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።
በምደባው ቅሬታ ያላቸው ተማሪዎች ደግሞ ቅሬታቸውን ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የኦንላይን ሥርዓት ብቻ https://student.ethernet.edu.et/complaints ይህ ምደባ ይፋ ከሆነበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን መረጃና ማስረጃ በማያያዝ እንዲያቀርቡ ሚኒስቴሩ ጠቁሟል፡፡
በአካል ወደ ተቋሙ በመምጣት የሚቀርብ የምደባ ቅሬታ የማይስተናገድ መሆኑን የገለጸው ሚኒስቴሩ፤ በተጨማሪም የተሳሳተ ማስረጃ ወይም የተጭበረበረ ሰነድ ማቅረብ በፍጹም የተከለከለ መሆኑን ተማሪዎችና ወላጆች እንዲገነዘቡ አሳስቧል፡፡

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: