Search

በትግራይ ክልል ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓትን ማረጋገጥ ይገባል፦ ስምረት ፓርቲ

ቅዳሜ መስከረም 09, 2019 31

የትግራይ ክልል አሁን ካለበት ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ውጥንቅጥ ወጥቶ ሀገራዊ ሚናውን እንዲጫወት፣ ወደ ሙሉ ሕገ-መንግሥታዊ መስመር መመለስ ቀዳሚ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ የስምረት ፓርቲ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሺሻይ አማረ (/) አሳሰቡ።

ዶክተር ሺሻይ ከኢቲቪ ትግርኛ ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ በትግራይ የሚገኘው አካል ለጦርነት የሚያበቃ ምንም ዓይነት አሳማኝ ምክንያት እንደሌለው ገልጸው፣ ቡድኑ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነትን ለፖለቲካ ፍጆታ ማዋሉን ተችተዋል።

በተጨማሪም የጦር መሣሪያዎችን እና ታጣቂዎችን በሲቪል ተቋማት ውስጥ በማከማቸት ሕዝቡን ለከፍተኛ አደጋ እያጋለጠ መሆኑን አውስተዋል።

በቡድኑ ሥር የሚገኙ ታጣቂዎች የመዋጋት ፍላጎት እንደሌላቸው እና አብዛኞቹ ሰላምን እንደሚሹ ያመላከቱት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባሉ፣ እነዚህን ታጣቂዎች እንደየ አሐዳቸው በተደራጀ መልኩ ወደ ሀገር መከላከያ ሠራዊት የሚቀላቀሉበትን መንገድ ማመቻቸት ወሳኝ መሆኑን አመላክተዋል።

የባሕር በር ተጠቃሚነትን በተመለከተ ሲናገሩም፣ የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ በሕግ፣ በታሪክ እና በፖለቲካዊ ዕይታ ሲገመገም ጠንካራ መሠረት ያለው መሆኑን ጨምረው አብራርተዋል።

በአብረሃ ካሣ

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: