Search

የወላይታ ብሔር የቋንቋ እና ባህል ሲምፖዚየም እየተካሄደ ነው

ቅዳሜ መስከረም 09, 2019 56

የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ "ጊፋታ" በዓልን አስመልክቶ የብሔሩ የቋንቋ እና ባህል ሲምፖዚየም እየተካሄደ ይገኛል።

የወላይታ ብሔር በራሱ የቀን መቁጠሪያ ቀመር አዲሱን ዓመት የሚቀበልበት የጊፋታ በዓል አብሮነትን፣ ምስጋናን፣ ደስታን፣ መተሳሰብን፣ ይቅርታን እና ፍቅርን የሚያንጸባርቅ የብሔሩ ዋነኛ መገለጫ ነው።

በዓሉ በዓለም አቀፍ የትምህርት፣ ሳይንስ እና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስነት ከተመዘገበ በኋላ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚከበር በመሆኑ ዝግጅቱ በልዩ ድምቀት እየተከናወነ ይገኛል።

በቋንቋ እና ባህል ሲምፖዚየሙ ላይ የኦሮሞ አባገዳዎች፣ ከፌዴራል እና ከክልል የተጋበዙ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እንዲሁም ከተለያዩ ክልሎች የመጡ ተወካዮች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

በአደባባይ የሚከናወነው የጊፋታ ዋና ዝግጅት በነገው ዕለት (መስከረም 10 ቀን 2019 .) "የትውልድ ቅርስን እንጠብቅ፣ የጊፋታን ውርስ እናስቀጥል" በሚል መሪ ቃል በድምቀት ይከበራል።

ጊፋታ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የትምህርት፣ ሳይንስ እና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስነት ካስመዘገበቻቸው ቅርሶቿ መካከል አንዱ ነው።

በትዕግሥቱ ቡቼ

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: