Search

ወጋገን ባንክ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከታክስ በፊት 4.3 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

ቅዳሜ መስከረም 09, 2019 40

ወጋገን ባንክ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከታክስ በፊት 4.3 ቢሊዮን ብር ትርፍ እና ከታክስ በኋላ 3.1 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማስመዝገቡን ይፋ አድርጓል።

የወጋገን ባንክ . የባለአክሲዮኖች 33 መደበኛ እና 16 አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ በሂልተን ሆቴል በመካሄድ ላይ ይገኛል።

የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ዋና ሰብሳቢ አቶ አብዲሹ ሁሴን እንዳስታወቁት፣ ባንኩ በበጀት ዓመቱ 16.4 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ ያገኘ ሲሆን፣ ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር 21 በመቶ ዕድገት አሳይቷል።

የባንኩ የተከፈለ ካፒታል 44 በመቶ ዕድገት በማሳየት 10.1 ቢሊዮን ብር መድረስ የቻለ ሲሆን፣ አጠቃላይ ሀብቱም 111.3 ቢሊዮን ብር መድረሱ ተገልጿል። በተመሳሳይ ከደንበኞች የተሰበሰበው የተቀማጭ ገንዘብ መጠን 23 በመቶ በማደግ 81.6 ቢሊዮን ብር መድረሱን ባንኩ አስታውቋል።

ለተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች የሰጠው አጠቃላይ የብድር መጠንም 67.3 ቢሊዮን ብር መድረሱ በጉባዔው ላይ ተጠቅሷል።

በተጨማሪም ባንኩ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 366 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማግኘት የቻለ ሲሆን፣ ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 34 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን አቶ አብዲሹ ጠቅሰዋል።

የዳይሬክተሮች ቦርድ ዋና ሰብሳቢው አክለውም፣ ባንኩ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በርካታ ፈተናዎችን በማለፍ ስኬታማ ጊዜን ማሳለፉን ገልጸው፣ ቀጣይነት ያለው ዕድገት እያስመዘገበ እንደሚገኝም አብራርተዋል።

በአባዲ ወይናይ

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: