የትምህርት ለትውልድ መርሐ-ግብር በትምህርት ዘርፍ የነበረውን የፋይናንስ ክፍተት በመሙላት ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለፁ።
የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሀገር አቀፍ የምክክር መድረክ በሐዋሳ ከተማ እየተካሄደ ነው።
በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የተጀመረውን ሰፊ ንቅናቄ ተከትሎ የሚያስፈልገውን ፋይናንስ በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ ለመሙላት እየተሠራ ነው ብለዋል።
በመረጃ አያያዝ ላይ ያለውን ክፍተት ለማረምም በ2018 የትምህርት ዘመን በአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ዲጂታል የመረጃ አያያዝ ተግባራዊ እንደሚደረግ ገልፀዋል።
የትምህርት ቤት ምገባ በትምህርቱ ዘርፍ ከፍተኛ ውጤት እንዲመጣ እያደረገ በመሆኑ በገጠሩ የሀገሪቱ አካባቢዎችም ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ሚኒስትሩ አሳስበዋል።
ለ2018 የትምህርት ዘመን የሚያስፈልጉ የትምህርት ግብዓቶችን ለማሟላት ከወዲሁ ሰፊ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑም ተጠቁሟል።
በአስረሳው ወገሼ
#ኢቢሲዶትስትሪም #ኢቲቪ #ትምህርትሚኒስቴር #አጠቃላይትምህርት