ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመደመር መንግሥት በተሰኘው አዲሱ መፅሐፋቸው ዙሪያ በሰጡት ቃለ-ምልልስ ኢትዮጵያ ለመላው አፍሪካውያን የብልፅግና ተምሳሌት ትሆናለች ብለዋል።
ኢትዮጵያ እየተገበረችው ያለው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ተጨባጭ ለውጥ እያመጣ፣ ኢኮኖሚውም እያንሰራራ በመሆኑ የኢትዮጵያ ብልፅግና አይቀሬ ነው ብለዋል።
ሀገር በሩን እየዘጋ፣ ቪዛ እየከለከለ፣ አትምጡብን እያለ ያለው ድሃ ስለሆንን ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የኢትዮጵያ የአሁኑ ዝግጅት ከራሷ ልጆች ተርፋ መሄጃ ላጡ ሁሉ አቃፊ ለመሆን የሚያስችላት ስለመሆኑም ገልፀዋል።
ኢትዮጵያ የጀመረችውን ትጨርሳለች፣ ከልመና ትላቀቃለች፣ የፀናች ሀገር ትሆናለች፤ ልጆቿ በሀገራቸው ፓስፖርት የሚኮሩበት ጊዜ ቅርብ ነው ብለዋል።
ይህ እንዲሆን ብልፅግና እና የመደመር መንግሥት አበክረው ይሠራሉ፤ ውጤቱንም ያለጥርጥር እንጨብጠዋለን ሲሉ ተናግረዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ።
የኢትዮጵያን ብልጽግና መጠራጠር አያስፈልግም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህ እውን እንዲሆን ግን መትጋት እንደሚያስፈልግ ነው ያሳሰቡት።
በመሐመድ ፊጣሞ
#EBC #ebcdotstream #PMAbiy #Medemer #Yemedemermengist