የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ሀገራት ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር የመከላከል ቡድን ጉባዔ ከነገ ጀምሮ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ተገለፀ።
የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት በጉባዔው ቅድመ ዝግጅት እና ፋይዳ ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል።
የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን አማረ፤ 21 አባል ሀገራት በፋይናንስ ደህንነት ተቋማት የተወከሉበት የቀጠናው ቡድን ጉባዔ ከነገ ነሐሴ 16 እስከ 24 እንደሚካሄድ ገልጸዋል።
የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ሀገራት ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር የመከላከል ቡድን 50ኛ የከፍተኛ አመራሮች ግብረ-ኃይል ስብሰባ፣ 25ኛ የሚኒስትሮች ምክርቤት ጉባዔ እና 8ኛው የመንግስትና የግል አጋርነት ምክክር ፎረም በነዚህ ቀናት እንደሚካሄድ ተጠቁሟል።
በሞላ ዓለማየሁ