Search

የመደመር ትውልድ ደፍሮ ካነሳቸው ጉዳዮች አንዱ ቀይ ባህር ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ሓሙስ ነሐሴ 15, 2017 146

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመደመር መንግሥት በተሰኘው አዲሱ መጽሐፋቸው ዙሪያ በሰጡት ቃለ-ምልልስ የመደመር ትውልድ ደፍሮ ካነሳቸው ጥያቄዎች አንዱ የቀይ ባህር ጉዳይ መሆኑን ገልፀዋል።

የቀይ ባህር ጉዳይ ዛሬ የተነሳ የሚመስላቸው ሰዎች መኖራቸውን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የቆየና በትውልድ ውስጥ ራሱን ችሎ የተቀመጠ ጉዳይ ነው ብለዋል።

ጥያቄው ኢትዮጵያ ከቀይ ባህር ማዶ ካሉ እህት ወንድሞቿ ጋር ያላት ግንኙነት አስፈላጊ መሆኑን እንደሚያሳይ ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የገለፁት።

የመደመር ትውልድ መፅሐፍ በጥቅሉ የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመፍጠር ከትውልድ ምን ይጠበቃል፣ ምን የቤት ሥራ አለ፣ ምን ቢከወን የላቀች ሀገር መፍጠር ይቻላል የሚለውን በዝርዝር ይዳስሳል።

በሴራን ታደሰ

#EBC #ebcdotstream #PMAbiy #Yemedemermengist #seaport