Search

1 ቢሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት የሶማሊ ክልል ፖሊስ አጠቃላይ ሆስፒታል ተመረቀ

እሑድ መስከረም 17, 2019 53

የሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ 1 ቢሊዮን ብር ወጪ የተደረገበትን የክልሉ ፖሊስ ሠራዊት አጠቃላይ ሆስፒታል ዛሬ መርቀው ከፍተዋል።

700 ሚሊዮን ብር ለግንባታው፣ 300 ሚሊዮን ብር ደግሞ ለሕክምና መሣሪያዎች ወጪ የተደረገበት ሆስፒታሉ በአጠቃላይ 200 የሚጠጉ ክፍሎች እንዳሉት ተገልጿል።

ለከባድና ቀላል ቀዶ ጥገና አገልግሎት የሚውሉ 9 ክፍሎች እና 10 አልጋዎችን ያካተተው ሆስፒታሉ፣ በተጨማሪም የከፍተኛ የጤና ክትትል ክፍል (ICU) እንዳለውም ተጠቅሷል።

ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ በሆስፒታሉ ምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር፣ የሆስፒታሉ ግንባታ ለጸጥታ ኃይሎችና ለቤተሰቦቻቸው የጤና እንክብካቤን ለማጠናከር ከሚከናወኑ ተግባራት መካከል አንዱ መሆኑን ገልጸዋል።

የክልሉ ብሎም የሀገሪቱ የጸጥታ ኃይሎች የኅብረተቡን ሰላም እንዲሁም የመሠረ ልማቶችን ደህንነት በመጠበቅ ረገድ የማይተካ ሚና እንዳላቸው ጠቅሰዋል።

ለዚህም ጥራት ያለው ልዩ እና ነፃ የጤና አገልግሎት ሊያገኙ እንደሚገባ መናገራቸውን የሶማሊ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመለክታል።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: