Search

የባሕር በር አልባዋ የዩጋንዳ ምሁር ምን አሉ?

ሓሙስ ነሐሴ 15, 2017 1202

በአፍሪካ 16 ሀገራት የባሕር በር የላቸውም፤ በዚህም ምክንያት ለወደብ ኪራይ ከፍተኛ ወጪ ያወጣሉ።

ከእነዚህ ሀገራት መካከል ደግሞ ኢትዮጵያ እና ዩጋንዳ ተጠቃሽ ናቸው።

ዩጋንዳዊው ምሑር ኦልዎ ፓትሪክ የባህር በር የሌላቸው ሀገራትን እና የባህር በር ባለቤት የሆኑትን በጋራ ፋይናንስ አገናኝ መሰረተ ልማቶችን በመገንባት የጋራ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ እንደሚችሉ ያስረዳሉ።

የባሕር በር የሌላቸው አዳጊ ሀገራት ዓለም አቀፍ ፎረም ላይ የተሳተፉት ኦልዎ ፓትሪክ፥ የባሕር በር የሌላቸው ሀገራት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ፤ ፕሮጀክቶችን በጋራ ማቀድና በትብብር መስራት አንዱ አማራጭ እንደሆነ ያነሳሉ።

ዩጋንዳ ከጎረቤቶቿ ኬንያ እና ታንዛኒያ ጋር በጋራ ተጠቃሚ የሚያደርጉዋቸውን ፕሮጀክቶች በትብብር እየሰሩ መሆናቸውን አንስተዋል።

ለአብነትም በጋራ ፋይናስ እየተገነባ ያለው ስታንዳርድ ጋውጅ የባቡር መስመርን አንስተው፤  ዩጋንዳ፣ ሩዋንዳ፣ ደቡብ ሱዳንን እና ኬንያን በማገኛነት የቀጠናውን ሀገራት ተወዳዳሪነት ለማሳደግ ትልቅ አስተዋፅ ይኖረዋል ይላሉ።

ወደ ወደብ አገናኝ መሰረተ ልማትን በጋራ በመገንባት፤ ሸቀጦችን በቀላሉ ወደ ወደብና ከወደብ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ በማድረግ የንግድ ግንኙነቶችን ለማሳደግ እንዲሁም በዓለም ገበያ ተወዳዳሪነትን ከፍ ለማድረግ ይቻላል ሲሉ ያስረዳሉ።  

አሁን ላይ ኡጋንዳ የባህር በር ባይኖራትም ከጎረቤቶቿ ከታንዛኒያ እና ከኬንያ በስምምነት እየተጠቀመች ነው ብለዋል፡፡

የባህር በር የሌላቸው ሀገራት ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ የጋራ ምክክርን፤ በጋራ ማቀድን እና በጋራ ሀብት ማፈላለግን ማጠናከር እንዳለባቸው ገልፀዋል።

ዕድሎችን በጋራ ፋይናንስ በማድረግ የባሕር በር የሌላቸው ሀገራትም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከእቅድ ጀምሮ እስከ ትግበራው በጋራ መሥራት አስፈላጊ መሆኑንም ነው የተናገሩት፡፡

 

 

በላሉ ኢታላ

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ተያያዥ ዜናዎች: