ሚዲያዎች ሰላምን ለማስፈን የሚደረጉ ጥረቶችን የብሔራዊ ጥቅም አካል አድርገው መስራት እንዳለባቸው የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሳምሶን መኮንን (ዶ/ር) ሚዲያው ሰላምን ዋና ተልዕኮ እና ራዕዩ አድርጎ መስራት ግዴታው ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡
ሚዲያዎች ረጅም የአየር ሰዓት ወስደው ስለሰላምን የመዘገብ ልምድ እንደሌላቸው አንስተው፤ ፤በሀገሪቷ የሰላም ጋዜጠኛ እራሱን ችሎ ሊኖር እንደሚገባ ነው የገለፁት ፡፡
ማንኛውን ሚዲያ ሲመሰረት ፍቃድ የምንሰጠው ስለሰላም ይሰራል ብለን ስናስብ ነው ብለዋል፡፡
የሚዲያውን ዘርፍ አቅም ለማሳደግም ታስቦ የሚዲያ ልኅቀት ማዕከል መገንባቱንም ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ ሚዲያ ልኅቀት ማዕከል ምስረታን አስመልክቶ ከተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ከተወጣጡ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡
በሜሮን ንብረት
#EBC #ebcdotstream #media