ቻይና በቤተሰብ ከአንድ ልጅ በላይ መውለድ የማይፈቅደውን “የዋን ቻይድ” ፖሊሲን ከቀየረች ቆይታለች።
በኋላም ከሁለት እና ሶስት ልጆችን በላይ መውለድ እንደማይገባ የሚያስገድዱ ፖሊሶዎችንም ተግብራ ነበር።
አሁን ግን ይህንንም ቀይራለች። ቻይና ዜጎቿ እንዲወልዱ ለማበረታታት እና የሕፃናት እንክብካቤን ለመደገፍ ለወላጆች ድጎማን እንደምታደርግ ይፋ አድርጋለች።
የቻይና የገንዘብ ሚኒስቴር እና የሀገሪቷ የግብር አስተዳደር፤ ከጥር 1 ቀን 2025 ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን አዋጅ አውጥተዋል።
በዚህም መሰረት ቻይና ለሕፃናት እንክብካቤ የሚሰጡ ድጎማዎች ከገቢ ግብር ነፃ እንዲሆኑ ወስናለች።
ቻይና ቤተሰቦችን ለመደገፍ እና ልጅ መውለድን ለማበረታታት የምታደርገው ሰፊ ጥረት አካል የሆነውን ብሔራዊ የሕፃናት እንክብካቤ ድጎማ ፕሮግራምን አስተዋውቃለች።
በፕሮግራሙ መሰረት ዕድሜያቸው ከሶስት ዓመት በታች ለሆኑ ሕጻናት ቤተሰቦች 3 ሺ 600 ዩዋን (504 ዶላር) ይሰጣቸዋል።
ይህም የወላጆችን ጫና ያቃልላል መባሉን ቻይና ዴይሊ ዘግቧል።
አዲሱን የቻይና ሕግ ዩኒሴፍን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት አወድሰውታል።
ቻይና የሕዝብ ቁጥሯ ከ1.4 ቢሊዮን በላይ መሆኑን እ.አ.አ. በ2024 አሳውቃ ነበር።
በሄለን ተስፋዬ