Search

የአፍሪካ ሀገራት ለእርስ በእርስ ንግድ ትኩረት በመስጠት የንግድ እንቅስቃሴዎያቸውን ሊያስፋፉ ይገባል - የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎዛ

ዓርብ ነሐሴ 16, 2017 94

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝደንት ሲሪል ራማፎዛ፥ የአፍሪካ ሀገራት ለእርስ በእርስ ንግድ ትኩረት በመስጠት የአህጉሪቱን የንግድ እንቅስቃሴዎች ማስፋፋት እንደሚያስፈልግ አስታውቀዋል። 

በጃፓን በተካሄደው ዘጠነኛው የቶኪዮ ዓለም አቀፍ የአፍሪካ ልማት ኮንፈረንስ ላይ የተገኙት ፕሬዚዳንቱ፥ የአህጉሪቱን የንግድ እንቅስቃሴዎች ከዚህም ባሻገር ወደተለያዩ ለም ሀገራት ለማስፋፋት በጋራ መስራት አለብን ብለዋል። 

ፕሬዚዳንቱ በጉባዔው ላይ ባደረጉት ንግግር አፍሪካ በአሁኑ ጊዜ እርዳታ እንደማትፈልግ ገልፀው፤ የአፍሪካ ሀገራት ዋነኛ ፍላጎት ዘላቂነት ያለው ልማትን እና የጋራ ኢንዱስትሪ መስፋፋትን ከሚረዱ የተለያዩ የዓለም ሃገራት ጋር አጋርነት መመስረት እንደሆነ ተናግረዋል። 

ሀገራቸው ደቡብ አፍሪካ በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ከተለያዩ ሀገራት ጋር ትብብሯን ለማጠናከር እንደምትፈልግም ፕሬዚዳንቱ መግለጻቸውን ኤስኤቢሲ ዘግቧል። 

አፍሪካ የሩቅ ምስራቋ ሀገር ጃፓንን እንደ ቁልፍ አጋሯ አድርጋ ትመለከታለች ያሉት ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ፥ በአፍሪካ እና ጃፓን መካከል ያለው አጋርነት የኢንዱስትሪ ዘርፍን ለማጠናከር እንደሚረዳም ነው ያነሱት።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ተያያዥ ዜናዎች: