Search

የምክረ ሐሳብ ርክክቡ ፈተናዎችን በሀገር በቀል መፍትሔ አምጪ እሴቶች ለመፍታት ያለንን ቁርጠኝነት በድጋሚ ያረጋገጠ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ቅዳሜ መስከረም 23, 2019 80

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት፣ ከኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር የተገኙ የአጀንዳ ነጥቦች እና ምክረ ሐሳቦች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ለፌደራል መንግሥት እንዲሁም ለክልል መንግሥታት ይፋዊ ርክክብ ተደርጓል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በፌስቡክ ማኅበራዊ ‎ትስስር ገፅ ባጋሩት መልዕክት፣ ይህ የሰነድ ርክክብ በራሱ በሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ውስጥ ጉልህ ምዕራፍ ነው ብለዋል።

የምክረ ሐሳብ ርክክቡ ኢትዮጵያውያን ዘላቂ ሀገራዊ ፈተናዎችን አካታች በሆነ ውይይት፣ በሰላማዊ ምክክር እና በራሳችን ሀገር በቀል መፍትሔ አምጪ እሴቶች ለመፍታት ያለንን ቁርጠኝነት በድጋሚ ያረጋገጠ ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: