ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመደመር መንግሥት ምሥረታን በማስመልከት መልካም ምኞታቸውን ለመግለጽ የተገኙትን የደቡብ አፍሪካውን ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛን በደስታ ተቀብለው ያነጋገሩ ሲሆን፣ ላስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክትም ምስጋና አቅርበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ይህንኑ በማስመልከት በማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ኢትዮጵያ እና ደቡብ አፍሪካ ለአፍሪካ አህጉር አንድነት፣ ሰላም፣ ልማት እና ብሩህ ተስፋ ባላቸው የጋራ ቁርጠኝነት ላይ የተመሠረተ ጠንካራ እና ታሪካዊ ግንኙነት እንዳላቸው ገልጸዋል።
ሁለቱ ሀገራት ያላቸውን ስትራቴጂያዊ አጋርነት ይበልጥ ለማሳደግ እና በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የቆየ የወዳጅነት ትሥሥር ይበልጥ ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላቸው አስታውቀዋል።
#ትልቅ_ሀገር! #ትልቅ_ሕዝብ! #ታላቅ_ርዕይ!
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: