Search

የኢጋድ ዋና ጸሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎ መልዕክት አስተላለፉ

ሰኞ መስከረም 25, 2019 134

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) ዋና ጸሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር)፣ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በድጋሚ በመሰየማቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።

ዋና ጸሐፊው በመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክታቸው ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ስኬታማ የሥራ ዘመን፤ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ደግሞ ቀጣይነት ያለው ዕድገት፣ አንድነት እና ብልፅግናን ተመኝተዋል።

ኢጋድ ከኢትዮጵያ ሕዝብ እና መንግሥት ጋር ያለውን የልማት ትብብር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸው፤ ተቋሙ ለምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ዘላቂ ሰላም እና የጋራ ብልፅግና ለመሥራት ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: