በደቡብ ቺሊ አቅራቢያ በሬክተር ስኬል 7.5 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ አመላክቷል።
የመሬት መንቀጥቀጡ የተከሰተው ከመሬት ወለል በ11 ኪሎ ሜትር ጥልቀት ላይ ሲሆን፤ በቺሊ እና በአርጀንቲና አንዳንድ ክፍሎች ላይ መንቀጥቀጡ ተሰምቷል።
የመሬት መንቀጥቀጡን ተከትሎ ቺሊ አንታርክቲክን በሚያዋስነው ግዛቷ በኩል አጭር የሱናሚ ማስጠንቀቂያ ብትሰጥም፤ በኋላ ላይ ምንም የሱናሚ ስጋት እንደሌለባት ተረጋግጧል።
በቺሊ እና በአከባቢዋ ላይ በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ እስካሁን ምንም አይነት ጉዳት አልደረሰም ሲል አናዶሉ ዘግቧል።