Search

በዓለም አቀፍ ሕጎች ላይ የተመሰረተው የኢትዮጵያ ፍትሐዊ የባሕር በር ጥያቄ

ዓርብ ነሐሴ 16, 2017 170

የተባሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ሕ የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ  የሚደግፍ መሆኑን የዲፕሎማሲ እና የዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁሩ ፕሮፌሰር ብሩክይሉ ገለፁ።

በዚሁ የተመድ እና መርህ መሰረት ተጠቃሚ የሆኑ እና የሚተዳደሩ በርካታገራት መኖራቸውንም ፕሮፊሰር ብሩክኢቢሲ አዲስ ቀን የዜና መሰናዶ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።

የኢትጵያ ጥያቄ በሌለ ነገር ላይ ሳይሆን በተመድ ሕግ በአንቀፅ ተለይቶ በተደነገገ እና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም ተስማምቶበት እየተጠቀመበት በሚገኝ እና መርህ ላይ የተመሰረተ ሕጋዊ ጥያቄ መሆኑን ገልፀዋል።

በዚህ ዓለም አቀፍግ እና ስምነት መሰረት እንደ ኢትዮጵያ ያለ ሀገር በአቅራቢያው ያለን ወደብ በሰላማዊ እና በዲፕሎማሲያዊ መንገድመጠቀም በሕግ እስከ መጠየቅ የሚደርስ መብት እንዳለው ነው ፕሮፌሰር ብሩክ ያብራሩት።

ኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄዋን እያቀረበች ያለችው በዓለም አቀፍ የባሕር በር ድንጋጌዎች እና በፍትሐዊነት ላይ ተመስርታ በሰላማዊ እና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ በመሆኑ ጥያቄው ፍፁም ተገቢነት ያለው መሆኑን አንስተዋል።

በመሆኑም እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በእያንዳንዱለም አቀፍ መድረክ ላይ የሀገሩ አምባሳደርመሆን የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተቀባይነት እንዲያገኝማስተጋባት ጀምሮ የሚቻለውን ሁሉ አስተዋጽኦ ማበርከት እንዳለበት ነው ፕሮፌሰር ብሩክ ያመላከቱት

በንፍታሌም እንግዳወርቅ

#EBCdotstream #ETV #Ethiopia #Seaport