የተፈጥሮ ጋዙ የተገኘው በመካከለኛው ቻይና ሁቤ ግዛት ውስጥ መሆኑን ቻይና አስታውቃለች፡፡
በአካባቢው የተገኘው አዲስ የጋዝ ክምችት በቀን እስከ 323 ሺህ ኪዩቢክ ሜትር ጋዝ ማውጣት የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡
የተፈጥሮ ጋዙ የተገኘበት ቦታ የነበረው መልከካ ምድራዊ አቀማመጥ እና የተነሳ የፍለቃ ሥራውን ውስብስብ አድርጎት የነበረ ቢሆንም በኋላ ላይ ግን የተገኘው ውጤት እጅግ አመርቂ እንደሆነ የፕሮጀክቱ ኃላፊዎች ተናግረዋል፡፡
በተለምዶ የሼል ጋዝ ተብሎ የሚጠራው የጋዝ አይነት ከሚቴን የጋዝ አይነቶች የሚመደብ ሲሆን በአብዛኛው ጊዜ በአለታማ ስፍራዎች ውስጥ የሚገኝ እና በብዙ ቦታዎች የማይገኝ ነው፡፡
በርካታ ጥቅሞች ያሉት ይህ ጋዝ ለኢንዱስትሪዮች ኃይል ለማቅረብ ይረዳል። በዚህም ኢንዱስትሪዎች ዝቅተኛ የካርበን ልቀት እንዲኖራቸው ያግዛል ሲል ሲጂቲኤን ዘግቧል።
በሃብተሚካኤል ክፍሉ