የመንግሥት ሰራተኞች ደሞዝ ጭማሪን ተከትሎ የሚደረግ ማንኛውም ዋጋ ጭማሪ ከባድ እርምጃ እንደሚያስወስድ የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገልፀዋል::
ምክንያታዊ ያልሆኑ የዋጋ ጭማሪ እንዳይደረግ ሰፊ የቁጥጥር ሥራዎች እየተደረጉ መሆኑንም ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።
በዚህም ከክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ጋር በቅርበት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል::
በሄለን ተስፋዬ