የአሸንድዬ፣ ሻደይ እና ሶለል በዓላትን ይበልጥ በማተዋወቅ ለቱሪዝም ገቢ መጠቀም ይገባል - የኢትዮጵያ ባህል እና ቱሪዝም ጋዜጠኞች ማህበር
**************
የአሸንድዬ፣ ሻደይ እና ሶለል በዓላትን ይበለጥ በማስተዋወቅ ከውጭ ሀገር ጎብኚዎች ተጨማሪ ገቢ መፍጠር እንደሚገባ የኢትዮጵያ ባህል እና ቱሪዝም ጋዜጠኞች ማኀበር ገልጿል።
የማኀበሩ ሥራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ አስናቀ ብርሀኑ በዓላቱ ውብ እና ድንቅ መሆናቸውን የሚናገረው ጋዜጠኛው ለዓለም ማህበረሰብ በተገቢው መንገድ እንዳልተዋወቀም ይገልጻል፡፡
በእነዚህ በዓላት በልጃገረዶች የየአካባቢውን ቱባ ባህላቸውን የሚያንጸባርቁበት በመሆኑ ጎብኚዎችን ለመሳብ ይጠቅማል ሲሉ አስረድተዋል።
በፋሽን ዲዛይን ውስጥ ያሉ ባለሙያዎችም ለበዓላቱ የሚለበሱ አልባሳትን በስፋት በማዘጋጀት ገቢያቸውን ማሳደግ እንደሚችሉ የማኀበሩ ሥራ አስኪያጅ ተናግረዋል።
በሜሮን ንብረት