Search

ዓለም አቀፉ የቴምር ፌስቲቫል - በሰመራ

ቅዳሜ ነሐሴ 17, 2017 36

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የቴምር ፌስቲቫል በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ይካሄዳል።

የአፋር ክልል ግብርናና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ ሀላፊ ኢንጅነር ያሲን አሊ፤ ፌስቲቫሉ ኢትዮጵያ ያላትን የቴምር ምርት ውጤታማነት ለማሳደግ አላማ ያደረገ መሆኑን አስረድተዋል።

ከተባበሩት አረብ ኢምሬት፣ ከሳዑዲ አረቢያ፣ ከግብፅ፣ ከዮርዳኖስ፣ ከሞሮኮ፣ ከፓኪስታን፣ ከሞሪታኒያ፣ ከሶሪያ፣ ከሜክሲኮ፣ ከኡዝቤኪስታን እና ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ 40 ዓለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ አጋር ድርጅቶች ይሳተፋሉ ብለዋል።

በተለይም የተባባሩት ዐረብ ኤምሬቶች በቴምር ምርት ላይ ያላትን ሰፊ ተሞክሮ ለመውሰድ እድል የሚሰጥ ፌስቲቫል መሆኑንም  አንስተዋል።

ፌስቲቫሉ የተሸሻሉ ቴክኖሎጂዎችን በማስተዋወቅ የቴምር ምርት እና ምርታማነትን ለማሻሻል ትልቅ እገዛ እንደሚያደርግ ይጠበቃል ሲሉ ቢሮ ሀላፊው ተናግረዋል፡፡

ፌስቲቫሉን የግብርና ሚኒስቴር፣ የአፋር ክልል እና መቀመጫውን በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች ያደረገው 'ካሊፋ ኢንተርናሽናል አዋርድ ፎር ዴት ፓልም ኤንድ አግሪካልቸር ኢኖቬሽን' በጋራ እንዳዘጋጁት ተገልጿል፡፡

መርሃ-ግብሩ ከነሐሴ 20 - 22 ቀን 2017 ዓ.ም በሰመራ ከተማ ይካሄዳል።

 

በሁሴን መሀመድ

#EBC #ebcdotstream #Afar #datepalm