Search

የአሶሳ ከተማ የኮሪደር ልማት ሥራ ውጤቱ የሚታይ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ቅዳሜ ነሐሴ 17, 2017 41

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአሶሳ ከተማ የኮሪደር ልማት ሥራ ውጤቱ የሚታይ መሆኑን ገለጹ።

ከአንድ ዓመት በፊት ወደ አሶሳ ሄደው እንደነበር የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ዛሬ በከተማዋ ያዩት ባለፈው ዓመት ካዩት በፍፁም ተቃራኒ ነው ብለዋል።

የተለወጠበት መንገድ ጥሩ ጅማሮ መሆኑን እና የኮሪደር ሥራ ውጤቱ የሚታይ እንደሆነ ገልጸዋል።

ከአሶሳ የተወሰኑ መቶ ኪሎሜትሮች ርቀት የሚገኘው እና በማሽን የታገዘ ዘመናዊ ፋብሪካ የኩርሙክ ወርቅ ፋብሪካ አስደናቂ የሥራ ውጤት ስለመኖኑም ጠቁመው፣ በሚቀጥለው ዓመት በግማሽ አቅሙ ማምረት ይጀምራል ብለዋል።

የክልሉን ሰፊ የወርቅ አቅምም እንደሚያሳይ እና ከባለፈው ዓመት ጉብኝታቸው በኋላ ያዩት ዕድገት የሚበረታታ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባፈሩት መልዕክት አመላክተዋል።

ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ በሚጠናቀቅበት ጊዜ በጎ ተጽዕኖው በመላው ክልሉ የሚታይ እንደሚሆን ነው የጠቀሱት።

መሰል ፕሮጀክቶች ከሌሎች ፕሮጀክቶች ጋር ተደምረው የሀገራዊ ብልጽግናችን መገንቢያ ጡቦች ናቸው ሲሉም አክለዋል።

ማዕድን በብዝኃዘርፍ የልማት ምልከታችን አንዱ ቁልፍ ዘርፍ ሆኖ ይቀጥላል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልም ለዚህ ርዕይ መሳካት ዐቢይ ሚና ያለው መሆኑን እያስመሰከረ እንደሚገኝ መስክረዋል።

#EBC #ebcdotstream #PMAbiy #Assossa #corrridordevelopment