Search

የኩርሙክ ወርቅ ፋብሪካ አስደናቂ የሥራ ውጤት ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ቅዳሜ ነሐሴ 17, 2017 49

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኘውን የኩርሙክ ዘመናዊ የወርቅ ፋብሪካ የግንባታ ሂደት ተመልክተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅትም፤ የኩርሙክ ወርቅ ፋብሪካ አስደናቂ የሥራ ውጤት ነው ብለዋል፡፡

መጀመር በቂ አይደለም ክትትል እና ድጋፍ ያስፈልጋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልልም ሆነ የአሶሳ ከተማ እየተለወጡ ያለበት መንገድ የሚታይ መሆኑን ገልፀዋል።

ባለፈዉ ዓመት ክልሉን ለመጎብኘት ሲመጡ የነበረዉ የከተማው ገፅታ በእጅጉ መቀየሩንና የኮሪደር ልማት ከከተማ ወጥቶ በክልል መታየቱ አስደሳች መሆኑን ተናግረዋል።

ከአሶሳ የተወሰኑ መቶ ኪሎሜትሮች ርቀት የሚገኘውና በማሽን የታገዘው ዘመናዊ የኩርሙክ ወርቅ ፋብሪካ አስደናቂ የሥራ ውጤት መሆኑንም ገልጸዋል።

ፋብሪካው የክልሉን ሰፊ የወርቅ አቅም ያሳያል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በምስራቅ አፍሪካ ትልቁ ፋብሪካ እንደሚሆንም ጠቅሰዋል፡፡

ፋብሪካው በሚቀጥለው አመት በግማሽ አቅሙ ማምረት እንደሚጀምር ገልጸዋል።

መሰል ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆናቸዉን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህም ከሌሎች ፕሮጀክቶች ጋር ተደምሮ የኢትዮጵያን ብልጽግና አዉን እንደሚያደረግ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ የብዝሀ ዘርፍ ኢኮኖሚ በመከተሏ በተለያዩ ዘርፎች ወጤት መታየቱንም አንስተዋል።

በቢታንያ ሲሳይ

#EBC #ebcdotstream #PMAbiy #Assossa