የትግራይ ክልል የፌዴራል መንግሥት ባለአደራ አስተዳደር ከመቐለ ከተማ ነዋሪዎች ጋር በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ህዝባዊ ውይይት አካሂዷል።
በውይይት መድረኩ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶችና የሃይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።
እንደ ኢዜአ ዘገባ የመድረኩ ዓላማ በክልሉ ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ከህዝቡ ጋር ለመወያየትና የተለያዩ ማኅበረሰባዊ ክፍሎችን በሚያሳትፍ መልኩ ሃሳብና አስተያየቶችን ለመለዋወጥ መሆኑም ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 62 ንዑስ አንቀጽ 9 እና በአዋጅ ቁጥር 359/1995 አንቀጽ 14 ንዑስ አንቀጽ 2(ለ) መሠረት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም ውሳኔ ማስተላለፉና ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ሥልጣን መስጠቱ ይታወሳል።
በዚሁ መሠረትም የፌዴራል መንግሥት ውሳኔውን ወደ ተግባር አስገብቷል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: