Search

የጉባ ብስራት ግዙፍ ፕሮጀክቶች ተቋማዊ ቁመና ይዘው በጥሩ መስመር ላይ ይገኛሉ፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ረቡዕ ጥቅምት 11, 2019 61

ጉባ ላይ የተበሰሩ እና ግንባታቸው የተጀመሩ ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ተቋማዊ ቁመና ይዘው ተስፋ ሰጪ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው በተለያዩ ዘርፎች እየተከናወኑ ያሉ ዋና ዋና ፕሮጀክቶችን አፈጻጸም አብራርተዋል፦

• የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ፦ የመጀመሪያው ምዕራፍ ሥራ በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ ሲሆን፣ በ3 እና 4 ወራት ውስጥ ተጠናቅቆ ሁለተኛው ምዕራፍ ይጀመራል።

• የጋዝ፣ ማዳበሪያ እና የነዳጅ ቧንቧ (ፓይፕ ላይን)፦ የጋዝ ምዕራፍ 1 ተመርቆ ምዕራፍ 2 ተጀምሯል፤ የማዳበሪያ ፋብሪካውም በከፍተኛ ሁኔታ እየተሠራ ነው። ጋዙን እና የማዳበሪያ ፋብሪካውን የሚያያይዘው የነዳጅ ቧንቧ እንዳለ ሆኖ፣ አሁን ደግሞ ከወደብ ወደ እዚያ የሚያመጣ ተጨማሪ መስመር ዝርጋታ ተጀምሯል።

• የመኖሪያ ቤት ግንባታ እና ፋይናንስ፦ በቤት ግንባታ ዘርፍ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እየገቡ ያሉ ሲሆን፣ የሞርጌጅ ባንክ ለመፍጠር የተጠናው ጥናት ተጠናቅቋል።

• የኑክሌር ተቋም፦ የኑክሌር አቅም ግንባታው ተቋማዊ መስመር ይዞ በጥሩ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ወላጆች ያገኙትን ሰብል በልተው እንደማይጨርሱ ሁሉ፣ ዛሬ ያገኘነውን ገቢ እና ብድር በልተን ሳናጠናቅቅ ለልጆቻችን ጥሪት፣ ሀብት እና መሠረት ማስቀመጥ አለብን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የታላቁ የመደመር ስትራቴጂ በሚቀጥሉት 25 ዓመታት ኢትዮጵያን በአፍሪካ ግንባር ቀደም ተምሳሌት እንደሚያደርጋት አረጋግጠዋል።

በዮናስ በድሉ

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: