Search

ደሴ ከተማ በኮሪደር ልማት

እሑድ ነሐሴ 18, 2017 85

ከተሞች እየተተገበረ በሚገኘው የኮሪደር ልማት ተደራሽ የሆነችው የደሴ ከተማ፤ አሁን ላይ ጥሩ የልማት እንቅስቃሴ ላይ የምትገኝ ከተማም ጭምር መሆኗ ይገለጻል።

በጦሳ እና በአዝዋ ተራሮች የተከበበችው የደሴ ከተማን የኢቲቪ ቅዳሜ አመሻሽ የዜና መሰናዶ ዳሰሳ አድርጓል 

የደሴ ከተማ አስተዳር ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝየደሴ ሕዝብ ሰላም ወዳድ ሕዝብ በመሆኑ የልማት ሥራዎች ላይ አተኩሮ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግራዋል 

የደሴ ከተማ የኮሪደር ልማት በነባር መንገዶች ላይ ብቻ ሳይሆን አዳዲስ የመንገዶች ግንባታን አካቶ በመከናወን ላይ ይገኛልም ነው ያሉት። 

የደሴ የኮሪደር ልማት ተሻጋሪ ድልድዮችን በመገንባት አዲስ እይታ የተንፀባረቀበት ጭምር ነው 

የመሶብ የአንድ መስኮት አገልግሎትን በደሴ ከተማ ለማስጀመርም በቀን እና በማታ ግንባታው በመከናወን ላይ መሆኑን ጠቅሰዋል። 

የደሴ ከተማ የኮሪደር ልማት ምዕራፍ አንድ ተጠናቆ 2018 ዓ/ም ምዕራፍ ሁለት ቀጣይነት እንደሚኖረውም ከንቲባው ለኢቲቪ ገልፀዋል

በንታሌም እንግዳወርቅ