ኢትዮጵያ በታሪኳ ያጋጠሟትን ማንኛውንም ፈተናዎች፣ የውስጥና የውጭ ተደራራቢ ጫናዎች በፅናት አልፋ የከፍታዋን ማማ የምትጨብጥ ታላቅ ሀገር ናት።
ለዚህ አኩሪ ሀገራዊ ፅናትና ሉዓላዊነት ደግሞ ዋነኛው መሠረት በቁርጠኝነት፣ በሙያዊ ብቃት እና በላቀ ሀገራዊ ፍቅር የታነፀው የአሸናፊው መከላከያ ሠራዊታችን የማይበገር ቁመና ነው።
በማንኛውም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ሀገርንና ሕዝብን የማስከበር ተልዕኮውን በላቀ ደረጃ የሚወጣው ሠራዊታችን፣ የመጣብንን ፈተና ሁሉ ወደ ታላቅ ሀገራዊ ድልና እምርታ የመቀየር የረጅም ዘመናት አሸናፊነት ታሪክ አለው።
ዛሬ ላይ በዘመናዊ ትጥቅና በቴክኖሎጂ ይበልጥ የተጠናከረው የሀገራችን መከታ፣ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም፣ ለልማታችን መረጋገጥ እና ለቀጣናው መረጋጋት አስተማማኝ ዋስትና ሆኖ ቀጥሏል።
በፅኑ ሠራዊታችን ታላቋን ኢትዮጵያ እናስክብራለን!
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: