የሀገር መከላከያ ሠራዊታችን የሀገራችንን ሉዓላዊነት፣ የሕዝባችንን ሰላምና ደኅንነት ለማስጠበቅ ሁሌም በፅናት የሚቆም ሀገራዊ አለኝታችን ነው።
የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እንዳሉት፣ ይህንን መስዋዕትነት ከፋይና ታላቅ ተቋም ማክበርና ድጋፍ መስጠት ሀገራችን ኢትዮጵያን የማክበርና የመውደድ ህያው መግለጫ ነው።
በማንኛውም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ የሀገርን ጥሪ የሚመልስ፣ ፈተናዎችን ወደ ድል የሚቀይር እና የዜጎችን እፎይታ የሚያረጋግጥ የመከላከያ ሠራዊት ባለቤት መሆናችን ትልቅ ሀገራዊ ኩራት ነው።
የሠራዊታችንን ዝግጁነትና ተቋማዊ ጥንካሬ ማጎልበት ለሀገራችን ዘላቂ ዕድገትና ለቀጣናው ሰላም አስተማማኝ መሠረት በመሆኑ፣ ሁላችንም ከጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን ጎን በመቆም አጋርነታችንን እናረጋግጣለን።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: