የትግራይ ክልል የፊዴራል መንግሥት ባለአደራ አስተዳደር ከአፄ ዮሐንስ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን ጋር መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደትን ማስጀመር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት አካሂደዋል።
በውይይቱ ወቅት መደበኛ ትምህርትን በተሳካ እና በተደራጀ ሁኔታ ለማስጀመር ትምህርት ቤቶች አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ሙሉ በሙሉ እንዲያሟሉ አቅጣጫ ተቀምጧል።
በተጨማሪም መምህራን እና ተማሪዎች በወቅቱና በጊዜው ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ፣ ሂደቱም ውጤታማ ይሆን ዘንድ መምህራን ንቁና ግንባር ቀደም ተሳትፏቸውን እንዲያረጋግጡ ጥሪ ቀርቧል።
ይህ ውይይት የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ እና የነገ ሀገር ተረካቢ ወጣቶችን ወደ እውቀት ማዕድ ለመመለስ በሚደረገው ሀገራዊ ጥረት ውስጥ ወሳኝ እርምጃ መሆኑ ተመላክቷል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: