Search

ሰሜን ኮሪያ አዲስ የአየር መከላከያ ሚሳኤል አስወነጨፈች

እሑድ ነሐሴ 18, 2017 49

ሰሜን ኮሪያ መሪዋ ኪም ጆንግ ኡን በተገኙበት ሁለት አዳዲስ የአየር መከላከያ ሚሳኤሎችን ለሙከራ አስወንጭፋለች።

ሙከራው ዛሬ በዋሽንግተን ዲሲ ይካሄዳል ተብሎ ከሚጠበቀው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የደቡብ ኮሪያው አቻቸው ሊ ጄ-ሚዩንግ የሁለትዮሽ ውይይት አስቀድሞ የተደረገ ነው።  

የሰሜን ኮሪያ ማዕከላዊ የዜና አገልግሎት እንደዘገበው፥ ሙከራው የአዳዲሶቹ የአየር መከላከያ ሚሳኤሎች የላቀ የውጊያ ብቃት የተረጋገጠበት ነው።

የመከላከያ ሚሳኤሎቹ በድሮን እና በክሩዝ ሚሳኤሎች ለሚሰነዘሩ የአየር ጥቃቶች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚያስችሉ ናቸው ተብሏል።

ሀገሪቱ አሁን ያስወነጨፈቻቸው አዳዲስ ሚሳኤሎች የአሠራር ሥርዓት በልዩ ቴክኖሎጂ ላይ የተመሠረተ ስለመሆኑም ተገልጿል።

በንፍታሌም እንግዳወርቅ

#EBCdotstream #NorthKorea #KimJongUn #airdefensemissiles