Search

12ኛው የአፍሪካ ደህንነት ጉባኤ ጣና ፎረም ተጀመረ

ቅዳሜ ጥቅምት 14, 2019 50

12ኛው የአፍሪካ ደህንነት ጉባኤ ጣና ፎረም “የሰላም መንገዶች በአፍሪካ፦ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት እና የጂኦፖለቲካዊ ሽግግር” በሚል መሪ ቃል በይፋ መካሄድ ጀምሯል።

ይህ መድረክ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎችን፣ ከፍተኛ ባለስልጣናትን እና ልዩ ልዩ ባለድርሻ አካላትን በአንድ ጃንጥላ ስር በማገናኘት ላይ ይገኛል።

 

በጉባኤው ወቅት ተሳታፊዎቹ በአህጉሪቱ ዘላቂ ሰላምና ደህንነትን ማስፈን፣ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ እንዲሁም ፈጣን ለውጥና ሽግግር በማሳየት ላይ ባለው ዓለም አቀፋዊ ሥርዓት ውስጥ አፍሪካ ሊኖራት ስለሚገባው ስትራቴጂካዊ ሚና እና ቀጣይ አቅጣጫዎች በሰፊው ይመክራሉ።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: